ኡጉይያ
Appearance
ኡጉይያ የሞሪታንያ ገንዘብ ስም ነው። በዚህ ገንዘብ አንድ ኢጉይያ አምሥት "ኩምስ" ማለት ነው። ኩምስ በአረብኛ አንድ አምሥተኛ ማለት ነው።
ሞሪታንያ በ ሲ. ኤፍ ኤ ፍራንክ እስከ ፲፱፻፷፮ ዓ.ም ስትጠቀም ከቆየች በኋላ በአምሥት ፍራንክ ምንዛሪ ገንዘቧን ወደ ኢጉይያ ቀየረች።
በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. ስሎቫኪያ በሚገኘው የክሮምኒካ ሳንቲም ፋብሪካ የተሠሩት የአንድ፣ አምሥት፣ አሥር እና ሃያ ሳንቲሞች ተሠራጩ።
በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. የአገሪቱ ብሔራዊ ባንክ በሙኒክ በሚገኘው ጊዬሽከ እና ደቭሪዬንት በሚባለው ማተሚያ ቤት የታተሙ የመቶ፤ ሁለት መቶ እና የሺህ ኡጊይያ ወረቀቶጭን አሠራጨ። ከስድስት ዓመት በኋላ፣ የ አምሥት መቶ ኢጉይያ ወረቀት ሲጨመር፤ በ ፲፱፻፺፫ ዓ.ም. ደግሞ የሁለት ሺህ ኢጉይያ ወረቀት ተጨምሯል።