Jump to content

አባል:የኢራን ባህል ማዕከል - ኢትዩጵያ

ከውክፔዲያ

የያልዳ ምሽት(ሻቢ፡ኤ፡ያልዳ)

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ኢራኖች በዓለማችን  ጥንታዊ ከሆኑት  ክብረ በዓላት አንዱ የሆነውን የያልዳ ምሽት(ሻቢ፡ኤ፡ያልዳ) በድምቀት ያከብራሉ።

ያለዳ ማለት መወለድ ማልት ሲሆን የሚያመለክተው  በአፈታሪክ የብርህይን አምላክ ሚትራን መወለድ ነው ይህ በዓል በያመቱ ታኅሣሥ 12 የአመቱ ረጅሙ እና የመጨረሻው ምሽት ተብሎ ይከበራል ።

በዚህ ምሽት የቤተሰብ አባላት በአንድ ላይ ተሰባስበው ያከብሩታል በበዓሉ ላይ ሮማንና ሐብሐብ ይቀርባሉ ብ ያለዳ ምሽት የሚቀርቡት ፍራፍሬዎች የየራሳቸው የሆነ ተምሳሌታዊ ትርጉም አላቸው

አን ዳንዶቹ ሐብሐብ ባለው ቅርፅ ፀሐይን እንደሚያመላክት ያመናሉ አንዳንዶች ደግሞ ሐብሐብ መብላት በክረምት ወቅት ከሚመጡ በሽታዎች ይከላከላል ብለው ያምናሉ ሮማንን ደግሞ የህይወትን፡ ኡደት እንደገና መወለደን ያመለክታል ተብሎ

ይታሰባል ።

በተለይ በያንዳንዱ ኢራናዊ ቤት ውስጥ መጽሐፉ የማይጠፋው የታዋቂውና ተወዳጁ ኢራናዊ ገጣሚ ሀፌዝን ግጥም በማምበብ  ጥሩና መልካም ምኞቶችን በመመኘት ይከበራል።