ቀለም
ቀለም | የሞገዱ ርዝመት | ድግግሞሽ ብዛት |
---|---|---|
ቀይ | ~ 700–635 nm | ~ 430–480 THz |
ብርቱካናማ | ~ 635–590 nm | ~ 480–510 THz |
ቢጫ | ~ 590–560 nm | ~ 510–540 THz |
አረንጓዴ | ~ 560–490 nm | ~ 540–610 THz |
ሰማያዊ | ~ 490–450 nm | ~ 610–670 THz |
ወይንጠጅ | ~ 450–400 nm | ~ 670–750 THz |
ቀለም |
(nm) |
(1014 Hz) |
(104 cm−1) |
(eV) |
(kJ mol−1) |
---|---|---|---|---|---|
አንስታይ ቀይ | >1000 | <3.00 | <1.00 | <1.24 | <120 |
ቀይ | 700 | 4.28 | 1.43 | 1.77 | 171 |
ብርቱካናማ | 620 | 4.84 | 1.61 | 2.00 | 193 |
ቢጫ | 580 | 5.17 | 1.72 | 2.14 | 206 |
አረንጓዴ | 530 | 5.66 | 1.89 | 2.34 | 226 |
ሰማያዊ | 470 | 6.38 | 2.13 | 2.64 | 254 |
ወይንጠጅ | 420 | 7.14 | 2.38 | 2.95 | 285 |
ተባታይ ወይንጠጅ | 300 | 10.0 | 3.33 | 4.15 | 400 |
በጣም ተባታይ ወይን ጠጅ | <200 | >15.0 | >5.00 | >6.20 | >598 |
የአይናችንን የተፈተለ እንዝርት የመሰሉ ጥቃቅን ክፍሎች የብርሃን ሞገድ ሲመታቸው፣ ይህ ጉዳይ ወደ አእምሮ ተላልፎ እንደተማቹ ብርሃን የሞገድ ርዝመትና ሃይል አይምሮአችን ወደ ቀይ አረንጓዴ እና ሰማያዊ መቺውን ብርሃን ይተረጉመዋል። ማስተዋል ያለብን እዚህ ላይ ቀለም በአይንና በብርሃን የሞገድ ርዝመት ብቻ የሚወሰን ሳይሆን አእምሮም ራሱ መጠነኛ ነው የማይባል አስተዋጾ ያደርጋል። ቢጫ ቀይና ሰማያዊ ቀለማት በአይን ይታዩ እንጂ እነዚህን 3 ቀለማት በማዋሃድ ህልቁ መሳፍርት የሆኑ የቀለም አይኖትችን እንድናይ የሚያደርገን አእምሮአችን ነው።
ብርሃን በራሱ የኮረንቲና ማግኔት ማዕበል ሲሆን ከዚህ ማእበል ውስጥ የሚታየው ክፍል ብቻ ብርሃን ይባላል። የማይታዩት ክፍሎች እንደነ ኤክስ ሬይ፣የራዲዮ ሞገድ፣ አንስታይ ቀይና ተባታይ ወይን ጠጅን ይጠቀልላሉ። እነዚህ እንግዲህ በአይን ስለማይታዩ በተለመዶ ብርሃን አይባሉም ምንም እንኳ የብራሃን ታላቅና ታናሽ ወንድም ቢሆኑም (ማለት በተፈጥሮአቸው አንድ አይነት ነገሮች ቢሆኑም)።
የኮረንቲና ማግኔት ማዕበል የሞገድ ርዝመቱ በትንሹ 390 ቢሊዮንኛ ከሜትር እና በትልቁ 650 ብሊዮንኛ ከሜትር (በቀላል አፃፃፍ ከ390 nm እስከ 750 nm) ከሆነ በዓይን ይታያል። በነዚህ የሞግድ ርዝመት ያሉ ብርሃናት በርዝመታቸው ልክ የተለያየ ቀለማትን ይወክላሉ። ( የቀኙን ሰንጠረዥ ይመልከቱ)።
ከቀኝ የተቀመጠው ሰንጠረዥ የሚያሳየው በቀስተ ደመና ውስጥ ሊገኙ የሚችሉትን ከአንድ የጠራ የሞገድ ርዝመት ካለው ብርሃን የሚሰሩትን ቀለማት ነው። ከበታች ያለው ሰንጠረዥ የየቀለማቱን የሞገድ ርዝመትና የሞገድ ድግግሞሽ በቁጥር ያሳየናል።
መረሳት የሌለበት የቀለማት ህብር አንድ ወጥ ሲሆን በተቆራረጠ የቀለም አይነቶች የምናይበት ምክንያት ከባህልና ያስተዳደግ ዘይቤ የተነሳ ነው። ምን ማለት ነው ኢትዮጵያ ያለ ሰው ቀይ ነው ብሎ የሚያምነውን አሜሪካ ያደገ ሰው ከነጭራሹ አላስፈላጊ ቀለም አድርጎ ሊቆጥረው ይችላል። ነገር ግን ሁሉም ህብረተሰብ ብርሃንን በአንድ አይነት የቀለም ህብር እንደሚከፋፍል ተደርሶበታል። ማለት አውሮጳዊውና ኢትዮጵያዊው ቀይ ነው ብለው የሚያስቡት ነገር አንድ አይነት ነገር ነው። [2]). በሁሉም ቦታ የሚሰራባቸው የቀለም ህብር ክፍፍሎች ስድስት ሲሆኑእነሱም ቀይ፣ ብርቱካን፣ ቢጫ፣ አረንጓዴ፣ ሰማያዊ እና ወይን ጠጅ ናቸው። ኢሳቅ ኒውተን በሰማያዊ እና በወይን ጠጅ መካከል ያለ ኢንዲጎ የተባለ ቀለም 8ኛ የሰወች ሁሉ የጋራ ቀለም ነው ቢሎ ቢጽፍም ቅሉ አሁን እንደተደረስበት አብዛኛው ህዝብ ይህን ቀለም ለይቶ ማየት ስለማይችል ከ6ቱ የጋራ መግባቢያ ቀለማት ሊባረር ችሎአል።
የቀለም ግንዛቤ በብርሃኑ ሞገድ ርዝመት ብቻ ሳይሆን አንድ-አንድ-ጊዜ በፈጠረው ብርሃንም ሃይል ይወሰናል። ለምሳሌ በጣም ደብዛዛ ብርቱካናዊ ቢጫ እንደ ቡኒ ሆኖ እንገነዘበዋለን፣ እንዲሁ ድብዝዝ ያለ ቢጫማ አረንጓዴ በአይን ሲታይ የኦሊቭ አረንጓዴ ይመስላል።
ያንድ ዕቃ ቀለም ቤእቃው ተፈጥሮ ብቻ ሳይሆን የሚወሰነው በተመልካቹም አይንና አእምሮ ጭምር እንጂ።
ከዚህ የሚክተሉት የቀለም አስተኔዎች ይህ አይነት ስያሜታ ሊይዙ ይቺላሉ። አስተኔ ማለት በስፊው ትርጉሙ ድብልቅ መጢቃ ክልስ ቅይጥ ማለት ነው። ሌላም ንግጝራዊ ዘይቤ አለው ግን አሁን ለቀለሞች መጠቀሚይ አድርገን እንውሰደው። አረጓዴ እና ፤የአርንጓዼ አስተኔ በጥቂቱ እነሆ.........ቀንበጥ -አረጓዼ የቢጫ ዘር በዉስጡ ያለው፡ ቡላ አርንጓዴ - የገረጣ አረጓዴ ፤ወይራ ፍሬ አርንጓዴ ፡ አልጌ አረንጓዴ ወይበራአርንጓዴ ወዘተ አስተኔው ድንበር የለዉም፡፡ የቢጫ- አስተኔ.......እርዴ ....ሎሚት...አደዮ.. አደይ አበባ የመሰለ....አብሺት.... አብሽ የመሰለ፡ ሰፈፌ፡ ሰፈፍ የመስለ:.....አፋር. ቢጫ ድኝቴ....ድኝ የሚመስል። የሰማያዊ አስተኔ......ክብረ ስማይ ስማያዊ ። ጉሎ ስማያዊ ፡፡ዉሃ ሰማያዊ፤ ኢንዲጎ፡ አኩዋ ማሪን ቱርኪዝ ቀይ አስተኔ .... ቀጋ ቀይ፡ አዋዝ ቀይ፡ ፍምቀይ፡ የጽጌረዳ ደም፡ ጃኖ ቀይ፡ በቾ ቀይ ፡ጥቁር ቀይ የዎይን ጠጅ አስተኔ፡ አጋሜት፡ ሸንኮሪት የቡና አይነት አስተኔ፡ መረሬ ቡና አይነት፡ ሸክሊት ቡና አይነት፡ ኡብራ ቡና አይነት፡ ዳማ ቡና አይነት፡ የሃመር አስተኔ ፡ ዎንዜ ጥሪ ሃመር፡ እንዲህ እያለ ሁልቆ -ምሳፍርት በሌለው ዝርዝር ይቀጥላል ይህ የቀለም ስያሜታ፡ ለሰአሊዎች ልዲዛይነርች ለአታሚዎች እንዲሁም ለሌሎች በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ማሳስብያ እትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የባህል ቤተሰቦች ፣ስለ ቀለም የራሳቸው አምልኮ እና ፍች ነበራቸው፡ ለምሳሌ ጥንት የሸማ ጥለት እንድሁ አይለበስም ነበር፣ ጥለቱ ትርጉም እና ፍች ነበረው። ሌላው የሸዋ ኦርሞዎች ትልቅ ዛፍ ግንድ ላይ ቀይ ጨርቅ በስፊው ጠምጥመው ያስሩ ነበር። አማሮች ከቤተስቦቻቸው አንድ ሰው ስያርፍ ለሶስት ቀናት ነጭ ፈትል እንደ ማተብ ይስሩ ነበር።ይህ የጠቀስኩት ምሳሌ፣ ብቁንጽል ነው አርስቱ እጅግ ስፊ ነው ፣ ብዙ የመስክ ስራ እና ምርምር ያስፈልገዋል።
3-ኒውትራል ቀለም
4--ግራጫ አስተኔዎች
5- የቶን አስተኔው ደርጃ፣ እርከንወይም ጋማ
7-ቀለም ማጻዳት ማንጣት
8-ቀለም ማጥቆር ማጥላት
9-ህሮማቲካዊ ቀለም
10- ፕሪሜር ቀለም የቀለም ዐእማድ
!!-ስብትራክቲቭ ቀለም መበጥበጥ
12-የሰአሊ መሰርታዊ ቀለም
13-የቀለም አውደ ሰንጠርዥ
14-ቀለም-አዘል ግራጫዎች-ወይም የ ሶስትዮሽ ቀለሞች 15-ኮፕሊሜንታር ቀለሞች 16-ቀዝቃዛ እና ሙቅ ቀለሞች 17- የቀለም ውሁደት ቀለ አርሞኒ 18-የቀለም ኮንትራርስት 19- ሲሙልታናዊ ኮንትራስት 20-ኮንፕሌሜንታር ቀለሞችን ማጻዳት ማንጣት 21-ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን ማጥቆር 22- ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን በኒውትራል ደጀን ባግራዉንድ ከላይ የተጠቀሱት የቀለም ባህሪዎች በዝርዝ እያንዳኑ ግንዛቤ ምን ማለት እንደሆነ ይተነተናል።
አን ት አልም.አይ አንት አልምት አንድምንም አቅ አይብልስ ምርት 7-ቀለም ማጻዳት ማንጣት 8-ቀለም ማጥቆር ማጥላት 9-ህሮማቲካዊ ቀለም 10- ፕሪሜር ቀለም የቀለም ዐእማድ !!-ስብትራክቲቭ ቀለም መበጥበጥ 12-የሰአሊ መሰርታዊ ቀለም
13-የቀለም አውደ ሰንጠርዥ
14-ቀለም-አዘል ግራጫዎች-ወይም የ ሶስትዮሽ ቀለሞች 15-ኮፕሊሜንታር ቀለሞች 16-ቀዝቃዛ እና ሙቅ ቀለሞች 17- የቀለም ውሁደት ቀለ አርሞኒ 18-የቀለም ኮንትራርስት 19- ሲሙልታናዊ ኮንትራስት 20-ኮንፕሌሜንታር ቀለሞችን ማጻዳት ማንጣት 21-ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን ማጥቆር 22- ኮንፕሊሜንታር ቀለሞቺን በኒውትራል ደጀን ባግራዉንድ ከላይ የተጠቀሱት የቀለም ባህሪዎች በዝርዝ እያንዳኑ ግንዛቤ ምን ማለት እንደሆነ ይተነተናል።
segera sewoch
- Bibliography Database on Color Theory Archived ማርች 8, 2008 at the Wayback Machine, Buenos Aires University
- Color, Contrast & Dimension in News Design Archived ሴፕቴምበር 15, 2008 at the Wayback Machine
- Comparative article examining Goethean and Newtonian Color Archived ኤፕሪል 3, 2007 at the Wayback Machine
- The Creation of Color in Eighteenth-Century Europe
- Why are things colored? Archived ጁን 12, 2010 at the Wayback Machine
- Color relationships Archived ፌብሩዌሪ 20, 2006 at the Wayback Machine
- Why Should Engineers and Scientists Be Worried About Color?
- Robert Ridgway's A Nomenclature of Colors (1886) and Color Standards and Color Nomenclature (1912) - text-searchable digital facsimiles at Linda Hall Library
- Search thousands of colors and create color palettes
- ^ Craig F. Bohren (2006). Fundamentals of Atmospheric Radiation: An Introduction with 400 Problems. Wiley-VCH. ISBN 3527405038. http://books.google.com/?id=1oDOWr_yueIC&pg=PA214&lpg=PA214&dq=indigo spectra blue violet date:1990-2007.
- ^ Berlin, B. and Kay, P., Basic Color Terms: Their Universality and Evolution, Berkeley: University of California Press, 1969.