Jump to content

ከውክፔዲያ

(ቻይንኛ፦ 泄) በጥንታዊ ቻይና የሥያ ሥርወ መንግሥት ዘመን ንጉሥ ነበር።

የቀርከሃ ዜና መዋዕል በተባለው ጽሑፍ ዘንድ፣ ለዘመኑ የተዘገቡት ድርጊቶች እንዲህ ናቸው፦ በ1769 ዓክልበ. ግድም አባቱ ማንግ ዓርፎ ሤ ተከተለው። በ፲፪ኛው ዓመት (1758 ዓክልበ. ግ.) የዪን ገዥ ዝሃይ ወደ ዮውዪ አገር ሲጎበኝ በዚያ መረንነት ስለ ሠራ፣ የዮውዪ ገዥ ምየንቸን አስገደለውና ሎሌዎቹን አባረራቸው። በ1754 ዓክልበ. ግ. የዝሃይ ተከታይ ወይ እና የሆ ገዥ ኃያላት አብረው ዮውዪን ወረሩና ምየንቸንን ገደሉ። በ1749 ዓክልበ. ግ. ንጉሥ ሤ የአሕዛብን አለቆች አከበረ፦ የ«ነጭ አሕዛብ፣ ጨለማ አሕዛብ፣ ቀይ አሕዛብ፣ ብጫ አሕዛብ» አለቆች አከበረ።

በ፳፭ኛው ዓመት (1745 ዓክልበ. ግ.) ዓረፈና ልጁ ቡ ጅያንግ ተከተለው። ።

ቀዳሚው
ማንግ
የሥያ (ቻይና) ንጉሥ ተከታይ
ቡ ጅያንግ